October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይሮቢ የሚያደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አለመሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኬኒያ ናይሮቢ የሚገኘው የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራተኞች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው ምክንያት ወደ ናይሮቢ የሚያደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አለመሆኑን አስታውቋል። አየር መንገዱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ በመግለፅ በክስተቱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል። ደንበኞች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል ስልክ ቁጥር በ+251 11 617 9900 ወይም በ 6787 በመደወል አልያም ናይሮቢ የሚገኘውን ትኬት ሽያጭ ቢሮ በአካል በመገኘት ማግኘት እንደሚቻል አየር መንገዱ አስታውቋል።

EBC