October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርናው ዘርፍ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተፕራይዞችን ለማደራጀት እና ወደ ስራ ለማስገባት ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሃንስ አያሌው (ዶ/ር) ተፈራርመውታል፡፡ ሚኒስቴሩ ሥራ ፈጣሪዎችን በማበረታታት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ከባንኩ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል፡፡ “በግብርናው ዘርፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በበቂ መጠን የሉም” ያሉት ሚኒትሯ፤ ስምምነቱ በመስኩ የበለጠ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሃንስ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ባንኩ ከሚኒስቴሩ ጋር በመሆን በተያዘው በጀት ዓመት ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ለመርሐ-ግብሩ በአጠቃላይ 43 ሚሊዮን ዶላር ሥራ ላይ እንደሚውል የገለጹት ዮሃንስ አያሌው (ዶ/ር)፤ ባንኩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ፋይናንሱን ተደራሽ እንደሚያደርግ አብራርተዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ ለስራ ዕድል ፈጠራ ፋይናንስ የሚያቀርብ ሲሆን በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራሽ እንደሚሆን መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

EBC