January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት አላት – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት አላት – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴOn Aug 30, 2024 342አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቅርቡ ከሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት ጋር የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊስ ዋና ማጠንጠኛው ከጎረቤቶቻችን ጋር ያላት ግንኙነት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገልጸዋል።አምባሳደር ታዬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት በኋላ ከሶማሊያ መንግስት ጋር የተፈጠሩ ልዩነቶችን ለማጥበብ ብትሰራም የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት ልዩነትን ማስፋት የአዘቦት ተግባራቸው ሆኗል ብለዋል።በኬንያ ናይሮቢና በቱርክ አንካራ ተከታታይ ምክክሮች መካሄዱን አስታውሰው፤ በኢትዮጵያ በኩል አሁንም የንግግር በሮች አለመዘጋታቸውን አስታውቀዋል።ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2005 ጀምሮ ሶማሊያ እንደሀገር እንድትቆም ዋጋ መክፈሏንና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም መስዋዕት መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡ሆኖም የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን መስዋዕትነት ከማጣጣል ተግባር መቆጠብ አለባቸው ሲሉም አንስተዋል።በሌላ በኩል በጋራ ሲደረግ የቆየው የጸረ ሽብር ትግል እንዲቀጥል በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት መኖሩንም አብራርተዋል።ከሶማሊያ ጋር ለዘመናት የቆየ ትስስሮች መኖራቸውን ገልጸው፤ ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እና የተሰበሩም ካሉ በመጠገን የኢኮኖሚና ባህል ትስስሮችን ማስፋትና ማጠናከር ላይ ኢትዮጵያ ታተኩራለች ሲሉ ገልጸዋል።አለመግባባቶች ሲፈጠሩም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላት ግንኙነት ከመንግስት ለመንግስት ግንኙነት ያለፈ የህዝብ ለህዝብ ትስስር ያለው ነው ብለዋል።በሶማሊያ በኩል በቀጣናው ፍላጎት ያላቸውን ሌሎች አካላት ለማስተናገድ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያቆሙም አሳስበዋል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ሱዳን ወደ ሰላም እንድትመለስ እስካሁን ስታደር የቆየችውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በመግለጫቸው አንስተዋል።

FBC