October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ስፖርት አሁን ከገባበት የውጤት ቀውስ ለማውጣት ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ ያሻል ተባለ

የኢትዮጵያ ስፖርት አሁን ከገባበት የውጤት ቀውስ ለማውጣት ጊዜያዊ ጥገና ወይም ጊዜያዊ የህመም ማስታገሻ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር ፕሬዝንት አቶ አስራት ወርቁ ገለፁ፡፡ የሀገሪቱ ስፖርት ታሟል የሚሉት አቶ አስራት፤ ስፖርቱ አሁን ካለበት ችግር ለማውጣት ስር ነቀል ለውጥ በማድረግ ስፖርቱን ለመታደግ የመንግስት እይታና ጣልቃ ገብነት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የሀገሪቱን የስፖርት ፖሊሲ ከማስተካከል፤ ለስፖርት ኢንቨስትመንት አስፈላጊውን ድጋፍና ጥቅማጥቅም ከማድረግ፤ አጋር አካላት ለስፖርት እድገት የሚያወጡት ወጪ እንደ ወጪ ተይዞላቸው ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ከማድረግ፤ ሀገሪቱ ያላት አቅም በሙሉ በመጠቀም ስፖርት በማሳደግ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንድትሆን የመንግስት ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል አቶ አስራት ወርቁ ፡፡ ስፖርት ጤናማና አምራች ትውልድ በመገንባት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ቁልፍ ሚና መጫወት ይችላል ያሉት አቶ አስራት፤ የሀገሪቱ ስፖርት ታሞ ቃሬዛ ላይ ነው፤ መንግስት በስፖርት ላይ ስር ነቀል ለውጥ ወይም አብዮት ማካሄድ አለበት ብለዋል፡፡