October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሚያስተምር አባት፣ የሚሰማ ምዕመን

ኢትዮጵያ የአማኝ ህዝቦች ሀገር ናት፡፡ ሁሉም ዜጋ ሊባል በሚችል ደረጃ ስለራሱ፣ ስለቤተሰቡ፣ ስለሀገሩ እና በቀጣዩ ዓለም ስላለው ዕጣ ፈንታ ወደ ፈጣሪው ይጸልያል፡፡ በየቤተ- ዕምነቱ ያለው ምዕመን ከፈጣሪው ጋር ያለውን ሕብረት ለማጠንከር በጾም፣ በስግደት እና በምጽዋት ይተጋል፡፡ የኃይማኖት አባቶች ቅዱሳን መጻሕፍትን እየገለጡ ለስጋም ለነፍስም የሚበጀውን የፈጣሪን ቃል ያስተምራሉ፡፡ ዝማሬው፣ ሕብረቱ፣ ስብከቱ፣ ተግሳጹ….ሁሉም በቦታው እንዳለ ነው፡፡ እጆች ለጸሎት ለመዘርጋት ሳይሰንፉ፣ ዓይኖች ለምሕረት ለማንባት ሳይደርቁ፣ ጆሮዎች ቃሉን ለማድመጥ ሳይሞሉ፣ እግሮች ለመንበርከክ ሳይዝሉ፤ ትውልዱ ከሥነ-ምግባር እሴቶች ገሸሽ እያለ የመምጣቱ ነገር ለብዙዎች ግራ ነው፡፡ ኢቢሲ ሳይበር የሥነ-ምግባር እና ግብረ-ገብ እሳቤዎችን አስመልክቶ የኃይማኖት መምህራንን አነጋግሯል፡፡