October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአሜሪካ አትላንታ የቦይንግ አውሮፕላን ጎማ ፈንድቶ ሁለት የጥገና ሰራተኞች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

ቦይንግ 757-232 የሚል የምርት መለያ ያለው አውሮፕላኑ የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ ንብረት ሲሆን በአትላንታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሶስት ቀናት የቴክኒክ ጥገና ሲደረገለት እንደነበር ተመላክቷል፡፡አውሮፕላኑ በጥገና ላይ በነበረበት ወቅት ጎማው በመፈንዳቱ ሁለት የጥገና ሰራተኞች ሲሞቱ በተጨማሪ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉም ተገልጿል።የአውሮፕላኑ የጎማ ፍንዳታ መንስዔ አለመታወቁን የገለጸው የአር ቲ ዘገባ፤ የቦይንግ አውሮፕላን በየጊዜው የሚያጋጥሙት የቴክኒክ ችግሮች በርካታ አደጋዎችን ከማስከተሉ ባለፈ ለደንበኞች ደህንነት ስጋት እየሆኑ እንደሆነ ጠቅሷል።