October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዘ ነው

ከዛሬ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ጀምሮ 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ተጀምሯል። ይህ የፍጆታ ዕቃ በዋናኝነት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተደረገ ነው ተብሏል። የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር እና በመኪና ተጭኖ ወደ አገራችን እንደሚገባ በጂቡቲ የኢትዮጵያ የኤምባሲ ያወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡