ጠቅላይ ምንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራ አኑረዋልለታሪካዊው የችግኝ ተከላ በዛሬዋ ታሪካዊት ቀን በተፈጥሮ ስጦታ፣ በማዕድን ሃብት እና ለም ምድር በሚታወቀው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተገኝተን አሻራቸውን እንዳኖኑ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አኑረዋል። በዛሬው ሁነት መጨረሻ በመላው ሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት የተከልናቸው ችግኞች ወደ 40 ቢሊዮን ይደርሳሉ። ባለፈው አመት ከተተከሉት ችግኞች 50 ከመቶው በምግብ ዋስትና፣ አፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆት ላይ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ የተተከሉ ነበሩ። በቀጣይም እንደ አባይ ተፋሰስ ባሉ አካባቢዋች ችግኞችን በመትከል የውሃ ጥበቃ ሥራን ልንደግፍ ይገባል ብለዋል።
Woreda to World
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።