October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በመወከል አቶ ያዕቁብ ፈቂ፤ ለጎፋ ዞን ዋና አሰተዳደሪ ዳግማዊ አየለ (ኢ/ር) አስረክበዋል፡፡ ከድጋፉ ውስጥ 10 ሚሊየን ብር ለተጎጂዎች አፋጣኝ እርዳታ፣ 15 ሚሊየን ብር ደግሞ አካባቢውን በዘላቂነት ለማልማት የሚውል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ተጎጂዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዞኑ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማውን ሐዘን በድጋሚ ገልጾ ለተጎጂዎች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

EBC