October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአሽንዳ በዓል እሴቱን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ እየተሰራ ነው – የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

የአሽንዳ በዓል ባህላዊ እና ኃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ እየተሰራ መሆኑን፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡ ቢሮው በዓሉን አስመልክቶ የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት አካሄዷል፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ አሸንዳን የቱሪስት መስህብ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ የአሸንዳ የካርኒቫል ሥነ-ሥርዓት መካሄዱ ታውቋል፡፡ በነገው ዕለትም የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች በተገኙበት የአሸንዳ በዓል በድምቀት እንደሚከበር ተመላክቷል፡፡