October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ

የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።ጉባኤውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን በ2016 በጀት ዓመት በዞኑ በርካታ ተግባራት በተሻለ ደረጃ የተፈፀሙ በመሆናቸውን ለዚህም ስኬት የአስፈጻሚ አካላትና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።ዋና አፈጉባኤው አያይዘውም ምንም እንኳን አመርቂ ተግባራት በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ቢሆንም አሁንም ሰፊ ርብርብና ትኩረት የሚጠይቁ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።ጉባኤዉ ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን የአስፈጻሚ አካላት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትን ጨምሮ የዞኑ የ2017 ጥቅል በጀት እና ሌሎችም የተያዙ አጀንዳዎች ዙሪያ በመወያየት ምክር ቤቱ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።