እ.ኤ.አ. ኦገስት 16 ቀን 2024 ዓ.ም. ጠዋት ከህንድ ሙምባይ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በዝግጅት ላይ ወደነበረ አውሮፕላን የሚጫኑ ሻንጣዎችን ይዞ ወደ አውሮፕላኑ በመጎተት ላይ በነበረ ጋሪ ላይ ከተጫኑ ሻንጣዎች በአንዱ እሳት መታየቱን አየር መንገዱ አስታውቋል። ክስተቱ ጋሪው ከራምፕ አካባቢ ወደ አውሮፕላኑ በመሄድ ላይ ሳለ እንደተከሰተም ነው የተገለፀው።ይህንንም ክስተት የተመለከቱ በሙምባይ ያሉ የደህንነት ፣ የጸጥታ እና የእሳት አደጋ ባለሞያዎች እሳት የያዘውን ሻንጣ በመለየት እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለዋል። አውሮፕላኑ አስፈላጊው ተጨማሪ የደህንነት ፍተሻ ከተደረገለት በኋላ እና አስጊ ነገር አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በረራውን አካሂዷል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሙምባይ ኤርፖርት ባለስልጣናትና የሚመለከታቸው አካላት የክስተቱን ምንጭ በመመርመር ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰው እንደሚያስታውቅ ገልጿል።
EBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ