October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኤርዶሃን የፍልስጤማውያንን ሰቆቃን የሚያባብስ የምዕራባውያን ድጋፍ ተቀባይነት የለውም አሉ

አባስ በዛሬው እለት በቱርክ ፓርላማ በመገኘት በፍልስጤም ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ያደርጋሉየፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ በአንካራ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር ተወያዩ።በዝግ የተካሄደው ምክክር “እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ እየፈጸመችው ባለው ጭፍጨፋ እና ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር” ብሏል የፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ጽህፈት ቤት።እስራኤል በሃማስን የጥቅምት 7 ጥቃት ተከትሎ በጋዛ የምትፈጽመውን ጥቃት አጥብቀው የሚቃወሙት ኤርዶሃን፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁንን ከአዶልፍ ሂትለር ጋር እስከማመሳሰል መድረሳቸው ይታወሳል።አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በሽብርተኛ ድርጅትነት የመዘገቡትን ሃማስም “የነጻነት ታጋይ” ነው በማለት ማወደሳቸውም አይዘነጋም።

Al-Ain