November 24, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

16 ወራት ያስቆጠረውን የሱዳን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ንግግር በጄኔቫ ተጀምሯል

የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ተወካዩን ቢልክም የሱዳን ጦር ባለመሳተፉ ፊት ለፊት ድርድር መጀመር አልቻሉም

አሜሪካ እና ሳኡዲ ባዘጋጁት የጄኔቫው የሰላም መድረክ ኤምሬትስና ግብፅ እየተሳተፉ ነውየሱዳን ተፋላሚ ጀነራሎችን ለማቀራረብ ያለመ ምክክር በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ተጀምሯል።በአሜሪካና ሳኡዲ መሪነት እየተካሄደ ባለው መድረክ ግን ዋነኛ ተፋላሚዎቹ አልተገናኙም።የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ (አርኤስኤፍ) ተወካዩን ወደ ጄኔቫ ቢልክም በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር ግን በድርድሩ አልሳተፍም ብሏል።በዚህም ምክንያት ሁለቱን ተፋላሚ ሀይሎች ፊት ለፊት ለማገናኘት የተያዘው እቅድ ሳይሳካ መቅረቱን በሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሬሎ ተናግረዋል።

Al-Ain

You may have missed