October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ማህበራዊየአውሮፕላን ጉዞ ቲኬት ሳይገዛ ወደ ሁለት ከተሞች የበረረው ሰው

ግለሰቡ ከጀርኗ ሙኒክ ወደ ስዊድን ስቶኮልም ያለምንም ወጪ ተጉዟል

ማህበራዊየአውሮፕላን ጉዞ ቲኬት ሳይገዛ ወደ ሁለት ከተሞች የበረረው ሰውግለሰቡ ከጀርኗ ሙኒክ ወደ ስዊድን ስቶኮልም ያለምንም ወጪ ተጉዟልአል-ዐይን 2024/8/14 13:50 GMTበመጨረሻም በፖሊስ የተያዘው ይህ አነጋጋሪ ሰው እንዴት ሊጓዝ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው የአውሮፕላን ጉዞ ቲኬት ሳይገዛ ወደ ሁለት ከተሞች የበረረው ሰው፡፡የኖርዌይ ዜግነት ያለው ይህ ስሙ ያልተጠቀሰው ሰው ከጀርመን ዋና ከተማ ሙኒክ ወደ ሀምቡርግ እና ስቶኮልም ያለ ምንም የጉዞ ቲኬት ተጉዟል፡፡ግለሰቡ የአውሮፕላን ቲኬት ሳይገዛ የጸጥታ ሀይሎች ሳይዙት ወደ ሁለት ከተሞች መጓዙ ግርምትን ጭሯል፡፡ግለሰቡ የተጓዘባቸው አውሮፕላን ጣቢያዎች ሰዎች ያለ ቲኬት ጉዞ እንዳይጓዙ የሚከለክሉ ሰው አልባ ቴክኖሎጂዎች በስራ ላይ የነበሩ ሲሆን ይህ ሰው እነዚህ ሁሉ አልፎ ለመጓዝ በቅቷል፡፡ዘግይቶ በተደረጉ ማጣራቶች ግለሰቡ ትክክለኛ የጉዞ ቲኬት ገዝተው ቸክ ኢን ሲያደርጉ ለቸክኢን ማሽኑ በቂ ጊዜ ሳይሰጥ ሰዎቹን ተከትሎ ወዲያውኑ አብሮ ወደ አውሮፕላኖቹ መቀላቀሉ ተረጋግጧል፡፡

Al-Ain