October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አቶ ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመሩ ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጡ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የመሬት መንሸራተት በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመሩ ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡ ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የክልሉ መንግስት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ኮሚቴዎችን በማቋቋም የአስቸኳይ ጊዜ ስራዎች ብሎም በዘላቂነት የሚፈጸሙ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል። በዚህም በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን÷ የተሰበሰበውን ሀብት በአግባቡ በመያዝ ደረጃውን የጠበቀ ስርጭት እና የአስተዳደር ስርአት መከተል እንደሚገባ አቶ ጥላሁን ተናግረዋል። በአደጋው የተጎዱ ሰዎች ቤተሰቦችን በዘላቂነት ለማስፈር እና መልሶ ለማቋቋም እየተከናወነ የሚገኘው የመኖሪያና የእርሻ ቦታ መረጣና ዝግጅት በጥናት የተደገፈ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። ሂደቱም የህዝቡን ተሳትፎ ያረጋገጠ እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

EBC