October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) በሶማሊያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ባለፈው የሰው ህይዎት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሊያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ባለፈው የሰው ህይዎትና ባስከተለው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በሶማሊያ ሞቃዲሾ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት በሰው ህይወት መጥፋት እና በደረሰው ጉዳት በጣም አዝነናል ብለዋል፡፡በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ከተጎጂዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና የሶማሊያ ህዝብ ጋር እንደሆኑም ነው አክለው የተናገሩት፡፡

FBC