October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ ከ14 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ይሠራጫል- ሚኒስቴሩ

ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ ከ14 ሚልየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በመላ ሀገሪቱ እንደሚሠራጭ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡በአዳማ ጉምሩክ ጣቢያ የተለያዩ መሰረታዊ ሸቀጦችን ጭነው የቆሙ ከ700 በላይ ተሽከርካሪዎች ዛሬ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሕግ መጨረሳቸውንም ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ምርቱ ለገበያው በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ በመወያየት የመፍትሔ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል፡፡በዚህም መሠረት የገበያ ሁኔታን በዘላቂነት ለማረጋጋጥ በመንግሥት ወጭ የተገዛው ከ14 ሚልየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በሚቀጥለው ሣምንት በመላ ሀገሪቱ ይሠራጫል ብለዋል፡፡ 468

FBC