October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ቱርክ ኢንስታግራም በግዛቷ እንዳይሰራ እግድ ጣለች

ይህ እርምጃ የተወሰደው የቱርክ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን የሀኒየህን ግድያ አስመልክቶ የወጡ የሀዘን መግለጫዎች ኢንስታግራም አጥፍቷል ሲሉ ትችት ከሰነዘሩ በኋላ ነው

ቱርክ ኢንስታግራም በግዛቷ እንዳይሰራ እግድ ጣለች።

ቱርክ የሜታው የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ኢንስታግራም በግዛቷ እንዳይሰራ እግድ መጣሏን የሀገሪቱ የኢንፎቴክ ተቆጣጣሪ በዛሬው እለት አስታውቋል።

ተቆጣጣሪው አካል እግድ የጣለበትን እና እግዱ እስመቼ እንደሚቆይ ግልጽ አላደረገም።

ይህ እርምጃ የተወሰደው የቱርክ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ፋህረቲን አልቱን ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ወሳኝ የሆነውን እስማኤል ሀኒየህ ግድያን አስመልክቶ የወጡ የሀዘን መግለጫዎች ኢንስታግራም አጥፍቷል ሲሉ ባለፈው ረቡዕ ትችት ከሰነዘሩ በኋላ ነው።

“ይህ ግልጽ እና ቀላል ነው፤ ሀሳብን መገደብ ነው” ያሉት የቱርክ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አልቱን ኢንስታግራም ለዚህ ድርጊቱ የተጣሰ ፖሊሲ ስለመኖሩ አልጠቀሰም ብለዋል።

የኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ በእግዱም ሆነ በአልቱን አስተያየት ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

AL AIN