October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው

ትራምፕ በመጪው ህዳር ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፔንሲልቬንያ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነው የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው። በደጋፊዎቻቸው መሃል በመድረክ ላይ ቆመው የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያሰሙ የተተኮሰባቸው ዶናልድ ትራምፕ፤ በጆሯቸው አካባቢ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተለቀቁ ምስሎች አሳይተዋል። በወቅቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የግድያ ሙከራውን ያደረገው ግለሰብ ህይወት ማለፉ ተነግሯል።ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአሜሪካው ኤንቢሲ ኒውስ ዘግቧል።ዶናልድ ትራምፕ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው ተብሏል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ክስተቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ጥቃቱን አውግዘዋል።አሜሪካ ውስጥ በኃይል የሚደረግ እንቅስቃሴ ቦታ የለውም ሲሉም ተናግረዋል።ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣናትና የዓለም ሀገራት መሪዎችም ጥቃቱን እያወገዙ መሆኑ ተዘግቧል።

EBC