October 5, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአርሲ ዞን የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

 በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አብዱልሃኪም ሙሉ በአርሲ ዞን የተገነቡ ፕሮጀክቶችን እየመረቁ ነው፡፡

ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጥራት ደረጃ እና ጊዜ ተገንብተው መመረቃቸውንም አቶ አብዱልሃኪም ገልጸዋል፡፡

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የኢተያ ገጠር ሽግግር ማዕከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው÷ ማዕከሉ በአካባቢው ያለውን የግብርና ግብዓት እሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብ እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል፡፡

የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ መንግሥቱ ረጋሳ በበኩላቸው በክልሉ ተመሳሳይ ሥድስት ማዕከላት መገንባታቸውን በመግለጽ÷ የማዕከላቱ መገንባት ለአርሶ አደሮችም ሆነ ለባለሃብቶች ከፍተኛ ጥቅም አለው ብለዋል፡፡

ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 1 ሺህ 61 ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ፕሮጀክቶች በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መሠራታቸውን የገለጹት ደግሞ አርሲ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኢብራሂም ከድር ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በዞኑ እየተመረቁ ለሚገኙ ፕሮጀክቶችም 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉ ተመላክቷል፡፡

FBC