October 5, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የታየው የሼድ መያዝ ምጣኔ እድገት በሌሎችም መደገም አለበት – ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር)

በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የታየው የሼድ መያዝ ምጣኔ እድገት በሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመድገም መስራት እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በዛሬው እለት የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሀገር በቀልና የውጭ ኢንቨስተሮችና ኩባንያዎች ወቅታዊ የምርት ሂደት ተመልክተዋል፡፡

ከምልከታቸውም ባሻገር ከኢንቨስተሮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በእለቱም የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የ11 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡

በቀጣይ 100 ቀናት በትኩረት መሰራት የሚገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ120 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ 19 የማምረቻ ሼዶች ያሉት ሲሆን ሁሉም የማምረቻ ሼዶች በሀገር በቀልና በውጭ ባለሀብቶች ተይዘዋል።

በፓርኩ በግላቸው የማምረቻ ሼዶችን መገንባት ለሚፈልጉ ኢንቨስተሮች አስፈላጊ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ የተሟሉላቸው የለሙ መሬቶች ይገኛሉ።

በዛሬው እለት በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከነበረው መርሐ ግብር ጎን ለጎን በኢንዱስትሪ ፓርኩ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

FBC