ከ120 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ መድኃኒቶችን በራስ ዐቅም ማምረት ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ዐውደ-ርዕይን መርቀው ከፍተዋል፡፡ይህን ተከትሎም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓቶችንና እና መድኃኒቶችን ለማምረት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ከማድረግ ጀምሮ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።እንዲሁም መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን አስቻይ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸውን በዐውደ-ርዕዩ ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል፡፡”ጤናችን በምርታችን” በሚል መሪ ሐሳብ የተከፈተውን ዐውደ-ርዕይ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾች ማኅበር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡ለሥድስት ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ ከ110 በላይ የዘርፉ አምራቾች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡
FBC
More Stories
የዘመኑን ዐርበኝነት እውን ለማድረግ ራስን ለመቻል በሚደረጉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ-መለስ ትጋት ከኹሉም ዜጎች ይጠበቃል። -የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዌኖ እንኳን ለ116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ምሥረታ ቀን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
በሸካ ዞን ቴፒ ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው በክልሉ የመጀመሪያ የሆነው የግል ጤና ጣቢያ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በተገኙበት ተመረቀ።