November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አምባሳደር ታዬ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ ጋር ተወያዩ።አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴና ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮችና በአፍሪካ ቀንድ አገራት የሰላም ማስከበር ጉዳዮች ዙሪያ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ተናግረዋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ የታዳጊ አገራት አጀንዳዎች በሆኑ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ የአቅም ግንባታ ድጋፎች እንዲሁም በዘላቂ ልማት ግቦች ማረጋገጥ ጉዳዮችም እንደተወያዩ አንስተዋል።አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ኢትዮጵያ ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ የምትሰጠውን ትልቅ ቦታ እንዲሁም በቀጣይ በሚካሄደው ‘summit of future’ የተሰኘውን ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተመለከተም ዝርዝር ውይይት ስለማድረጋቸው ጠቅሰዋል።አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ በሚደረግ ጥረትና መሰል የፀጥታ ጉዳዮችም የውይይቱ አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት ማድነቃቸውን ቃል አቀባዩ አንስተዋል።መንግስት ውስጣዊ ግጭቶች በሰላም እንዲፈታ የያዘውን ቁርጠኛ አቋም ማድነቃቸውንም እንዲሁ ።ለልማት እንቅስቃሴዎችም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ስለመሆኑም አንስተዋል።

You may have missed