November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፑቲን ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጡ

ሩሲያ በ2022 ልዩ ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት በምስራቅ እና በደቡብ ዩክሬን ያሉትን እነዚህን አራት ግዛቶች የግዛቷ አካል አድርጋ አካታዋለች

ፑቲን ሩሲያ ጦርነት የምታቆመው ኪቭ ወደ ኔቶ የመቀላቀል ጥያቄዋን የምትተው እና ሞስኮ ይገቡኛል የምትላቸውን አራት ግዛቶች ለመስጠት ከተስማማች ብቻ ነው ብለዋል

 ፕሬዝደንት ፑቲን ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል።

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ጦርነት የምታቆመው ኪቭ ወደ ኔቶ የመቀላቀል ጥያቄዋን የምትተው እና ሞስኮ ይገቡኛል የምትላቸውን አራት ግዛቶች ለመስጠት ከተስማማች ብቻ ነው ብለዋል።

ይህን የሩሲያ ቅድመ ሁኔታ መቀበል እንደ “እጅ መስጠት” ይቆጠራል ያየችው ዩክሬን ወዲያውኑ ነው ውድቅ ያደረገችው።

ፑቲን፣ ሩሲያ በተገለለችበት እና በኪቭ አማካኝነት በስዊትዘርላንድ በተዘጋጀው የሰላም ጉባኤ ዋዜማ ላይ ከፍተኛ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጫቸው ጦራቸው የበላይነት እንደያዘ መተማመናቸውን ያሳያል ተብሏል።

ፕሬዝደንቱ ዩክሬን ትጥቅ እንድትፈታ መፈለጋቸውን እና ይህም በፈረንጆቹ የካቲት 2022 ጦራቸውን ወደ ዩክሬን በላኩ ወቅት ከያዙት አቋም ፈቅ እንዳላሉ የሚያመላክትም ነው። ፑቲን የምዕራባውያን ማዕቀብ መነሳት የስምምነቱ አካል እንዲሆን እንደሚፈልጉም ገልጸዋል።

ፑቲን ከቪ ከናዚ እንድትጸዳ ጥሪ ቢያቀርቡም፣ ኪቬ ግን በአመራሮቿ ላይ የተቃጣ መሰረተቢስ ስድብ ስትል ገልጻዋለች።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት አማካሪ የሆኑት ማይክሄሎ ፑቲን ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ ለዩክሬን መሸነፏን እንደማመን እና ሉአላዊነቷን ፈርማ እንደመስጠት ይቆጠራል ብለዋል።

አማካሪው ፑቲን ባሉት መሰረት “ስምምነት ላይ ለመድረስ እድል የለም” ሲሉም አክለው ተናግረዋል።

ፑቲን ይህን ንግግር ያሰሙት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ዩክሬን ላስቀመጠችው የሰላም ቅድመ ሁኔታ አለምአቀፍ ድጋፍ ለማስባሰብ ባዘጋጀችው የሰላም ጉባኤ ላይ ጥላ ለማጥላት ነው የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል።

“ሁኔታዎቹ በጣም ቀላል ናቸው” ያሉት ፑቲን የዩክሬን ጦር ከዶኔስክ፣ከሉሀንስክ፣ ከኬርሶን እና ከዛፖርዦያ ግዛቶች ሙሉ በመሉ መውጣት አለበት ብለዋል።

ሩሲያ በ2022 ልዩ ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት በምስራቅ እና በደቡብ ዩክሬን ያሉትን እነዚህን አራት ግዛቶች የግዛቷ አካል አድርጋ አካታዋለች።

 ሩሲያ ግዛቶቹን በከፊል የያዘች ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ ያላትን አላማ ለማሳካት ማጥቃቷን ቀጥላለች።

ሩሲያን ከግዛቷ ማስወጣት እንደምትችል የምትገልጸው ኪቪ ከምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፎች ጠይቃ እየቀረበላት ይገኛል።

ዩክሬን በስዊስ ያዘጋጀችው የሰላም ጉባኤ በርካታ አለምአቀፍ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ቢገለጽም፣ የሩሲያ አጋር እንደሆነች የሚነገርላት ቻይና እንደማትሳተፍ ገልጿል።

ቻይና ለዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት መፍትሄ ይሆናል ያለችውን የሰላም እቅድ ያቀረበች ሲሆን እቅዱ በሩሲያ በኩል ተቀባይነት አግኝቷል።

ፑቲን ቻይና ያቀረበችው እቅድ ከጦርነቱ በፊት ያሉ ሁኔታዎችን ከግምት የሚያስገባ በመሆኑ እንደሚቀበሉት መናገራቸው ይታወሳል።

Al-Ain

You may have missed