October 5, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት ያድጋል – ናሬንድራ ሞዲ

 በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት እንደሚያድግ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡

በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ናሬንድራ ሞዲ ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) ላስተላለፉላቸው መልዕክት አመስግነዋል፡፡

አጋር እንደመሆናችን መጠን ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።

አክለውም ፥ በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት ያድጋል ሲሉም ቃል ገብተዋል፡፡

FBC