October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ዋናው መቀመጫው እና የተመሠረተበት ሀገር ደቡብ ኮሪያ ከሆነው ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት መደረሱን የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈርው መልዕክት አስታውቋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በመልዕክቱ እንደገለጹትም፤ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ጋር በፅሕፈት ቤታቸው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ለመደገፍ እና በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም ወደ ስራ የሚያስገባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ነው ቀዳማዊት እመቤቷ የጠቀሱት፡፡

EBC