October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የልዩነት መፍቻ መንገድ ውይይት ብቻ መሆኑን በማሳየት ፋና ወጊ ሚናችሁን እንደምትወጡ ትልቅ ተስፋ አለን” – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወክለው በምክክር መድረኩ ላይ በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሀገራዊ ምክክሩ መሳተፍ ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነት ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ የመዲናዋ ነዋሪዎች ከማንኛውም የግልና የቡድን ስሜት እና አመለካከት በመውጣት በምክክሩ በንቃት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው፥ ለዘመናት ልዩነቶችን በሃይልና በጠመንጃ ከመፍታት ታሪክ በመውጣት በሰለጠነ መንገድ በውይይት ለመፍታት የሚያግዘን ሃገራዊ ምክክር በርዕሰ መዲናችን አዲስ አበባ መጀመሩ ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል።

እንደ ሃገር ያሉንን በርካታ መልካም ነገሮቻችንን በሚያጠለሽ መልኩ መጥፎ ገፅታችን ከነበረው ልዩነቶችን በጠመንጃ እና በጉልበት ከመፍታት እና የአንድ ሃገር ህዝቦች በዚህ ልክ በጠላትነት ከመፈራረጅ ተላቅቀን ልዩነቶቻችንን በውይይት ብቻ በመፍታት በሃገራችን ዘላቂ ሰላም እንድናሰፍን ምክክሩ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ይህ ለሃገራችን ተጨማሪ ታሪክና ታላቅ ውጤት የሚያስገኘው ሃገራዊ ምክክር፣ ህዝባችን የስልጣን እና የጉዳዩ ባለቤት በመሆን ራሱ በቀጥታና በመረጣቸው ተወካዮቹ አማካኝነት አጀንዳዎችን አቀራራቢ በሆነ መንገድ በምክክር በመፍታት ሃገራዊ መፍትሄ እንደሚያመጣ ይጠበቃል ነው ያሉት።

FBC