April 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ትዕግስት አሰፋ በዓለም አቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝገብ እውቅና ተሰጣት

በለንደን ማራቶን ክብረ ወሰን በመስበር ያሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ ከዓለም አቀፉ የድንቃድንቅ መዝገብ (World Guinness Book of Record) እውቅና ተሰጥቷታል።

በሴት አሯሯጮች ብቻ ወይንም ወንድ አሯሯጭ በሌለበት በዓለም አትሌቲክ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው ማራቶን ትዕግስት 2 ሰዓት 15 ደቂቃ 50 ሰከንድ በመግባት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።

በአንተነህ ሲሳይ