April 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

ማሻ ፣ የሚያዝያ 20፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በሸካ ዞን የማሻ ከተማ አስተዳደር ጤና ተቋማት የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ ግምገማዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄዷል።

መድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማሻ ከተማ ብልጽግና ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ አቶ አስማማው ነቺቶ ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከል ባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት በመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በመግለጽ በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ እየታዩ ያሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩ የግምገማ ሰነድ ያቀረቡት የማሻ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ክቡርሰዉ አለሙ የመንግስት የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት እየታዩ ያሉ የተለያዩ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል።

እነዚህም ከሆስፒታል ጀምሮ እስከ ጤና ኤክስቴንሽን ያሉ የግኑኝነት አግባብ መላላት፣ ለህክምና የሚረዱ የግብአቶች እጥረት፣ የአስተዳደራዊ ችግሮች፣ የፍላጎት እና የአቅርቦት አለመመጣጠን፣ ባለሙያዎች ስነምግባር፣ የአንቡላንስ አገልግሎት አሰጣጥ እና በዘርፉ ላይ ያሉ ዉስንነቶችን ለመፍታት መድረኩ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

ችግሮችን ለመፍታት የመሪነት ሚናን ማሻሻል፣ የግብአት እና የፋይናንስ ማነቆዎችን መለየትና መፍታት እንድሁም በህብረተሰቡ ዘንድ የኔነት ስመት መፍጠር እንደሚገባ አቶ ክቡርሰዉ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የዞኑ ደጋፊ ባለሙያዎች፣ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ የጤና ጣቢያ ባለሙያዎች፣ እንድሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።