ማሻ ፣ የሚያዝያ 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የኢራን ቁልፍ ወደብ በሆነው ሻሂድ ራጃኢ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ 800 የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል።
በፍንዳታው 6 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁም ነው የተጠቆመው።
አደጋው ከተነሳበት ስፍራ እስከ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ያሉ ተሽከርካሪዎች እና ህንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ነው የተጠቆመው።
“ፍንዳታው ለኢራን ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ጥቅም ላይ እንዲውል የታሰበው የሶዲየም ሮኬት ነዳጅ ወይም ሶዲየም ፐርክሎሬት የሚባለው ኬሚካል በትክክል ባለመጫኑ ሳቢያ የተከሰ ነው” ሲል የዓለም የባህር ስጋት አስተዳደር ድርጅት አምበሪ ኢንተለጀንስ አስታውቋል።
አምበሪ ኢንተለጀንስ ከዚህ ቀደም በሻሂድ ራጃኢ ያለውን አግባብነት የጎደለው የኬሚካል አቀማመጥን በተመለከተ ማስጠንቀቂያን ሰጥቶ እንደነበርም አስታውሷል።
ጭነቱን በተመለከተ የፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ሁለት የሶዲየም ሮኬት ነዳጅ የጫኑ መርከቦች ከቻይና ወደ ኢራን መግባታቸውን አመላክቶ ነበር።
አደጋውን ተከትሎ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በአደጋው ለተጎዱ እና ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።
በዚህም ፍንዳታው የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከተነሳ በኋላ ተቀጣጣይ ቁሶችን በውስጣቸው በያዙ እና ያልተዘጉ ወደ ነበሩ ኮንቴነሮች መዛመቱን ተከትሎ መሆኑን ጠቅሷል።
አሜሪካ ኢራን የራሷን የኒኩሌር ኃይል እንዳታበለፅግ ለማድረግ ውይይቶችን እያካሄደች ባለበት ወቅት የተከሰተው አደጋው ሀገራቱን ውጥረት ውስጥ የሚያስገባ ሊሆን ይችላል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።
ኢቢሲ
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ