April 7, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

272 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

ማሻ ፣ የመጋቢት 29፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) 272 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከመጋቢት 18 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 187 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የገቢ እና 84 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ማዕድናት፣ አልባሳት፣ ቡና፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድሃኒትና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ ነበር የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎች እና 7 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋና