ማሻ ፣ የመጋቢት 29፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በ2017/18 የምርት ዘመን ወደ ሀገር ለማስገባት ከታቀደው 24 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እስከ ትናንት ድረስ ከ10 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ ተገለጸ፡፡
55 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብም ጅቡቲ ወደብ ደርሳ ማራገፍ መጀመሯን የማሪታይም ባለስልጣን መረጃ አመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው ከ10 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታሉን ወደ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ መቻሉ ተገልጿል፡፡
More Stories
ሶስተኛው የአፍሪካ የማዕድን ፎረም ዛሬ ይጀመራል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን የቢዝነስ ጀት አውሮፕላን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ ተቀባይነቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል