መጋቢት 23፣ 2017 ያለፉት የለውጥ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ አካታችነትና አቃፊነት የተረጋገጠበት መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ተናገሩ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የምትስማማ፣ የእኩልነት እና የፍትሐዊነት መብትን በአግባቡ የምታስከብር እንድትሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊ ሀገር በመሆኗ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመመስረት ሁሉንም ማቀፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት አቶ አደም ፋራህ።
ብልጽግና ደግሞ ለዚሁ የተወለደ፣ ብዙ ክልከላዎች ያስቀረ እና ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ ያቀፈ ፓርቲ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
የዴሞክራሲ እጦት ባለፈው ስርዓት ችግር እንደነበር አንስተው በዚሁ ምክንያትም የፖለቲካ ለውጥ መምጣቱን አንስተዋል።
ለውጡ የህዝቡ የዘመናት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አስችሏልም ያሉት አቶ አደም ፋራህ፤ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያለምንም ልዩነት የሚያስተናግድ አውድ የተከፈተበት መሆኑን አመላክተዋል።
በሀገራችን የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ የብልጽግና መወለድ ትልቅ ክስተት እንደሆነ አንስተው፥ ሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ፕሮግራም ቀርፀናልም ብለዋል።
(ኤፍ ኤም ሲ)
More Stories
የዘመናት የማሻ ከተማና አካባቢው ህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት አቅርቦት ችግር የሚፈታ የሳብስቴሽን ግንባታ አልቆ መብራት የማብራት ሙከራ ስራ በስኬት ተጠናቀቀ
የሸካ ንጉስ ቴቺ ቄጃቺና የምክራቾ አባላት በማሻ ወረዳ ከሚገኙ የጎሳ መሪዎች ጋር ዉይይት አካሄዷል።
ኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን “አዲስ ምዕራፍ” ፕሮግራም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ