April 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሀገራዊ ለውጡ ከተረጅነት ወደ አምራችነት የሚያሸጋግር መሰረት መገንባት ጀምሯል- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ና የግብርና ቢሮ ሃላፊው አቶ ማስረሻ በላቸው

ማሻ ፣ የመጋቢት 20፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የመጋቢት ወር ታሪክና ትውልድ የሚዘክረውን አሻራ ያኖርንበት ወቅት ነው ይላሉ አቶ ማስረሻ የለውጡ ትሩፋቶችን ባወሳው ማብራሪያቸው ።

የዚህ ታሪክ ትውልድ ዕድለኛ መሆኑን በመግለጽ ።

ዛሬ ለተመዘገቡ ድሎች ዕውቅና ለመስጠት ትናንትን በልኩ መረዳት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል ።

ሀገሪቱ መሸከም በማትችላቸው ውስውስብ ችግሮች ተጠልፋ በመውድቅ አፋፍ ላይ ደርሳ እንደነበር ያወሳሉ አቶ ማስረሻ በአመራር ልምድና ብስለት በታጀበው ገለጻቸው

በሁለት እግሩ ሳይቆም ሀገርን ከገባችበት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ በማውጣት አንገቷን ቀና በማድረግ ወደ ቀደመው ከፍታዋ ለመመለስ ገና ከጅምሩ ያለመው የለውጡ መንግስት ባለፉት ቅርብ አመታት ባደረገው ርብርብ የሚተረኩ ሳይሆኑ የሚጨበጡ ድሎችን ማስመዘገቡን አውስተዋል።

የሀገር ሉኣላዊነት ዳር ድንበርን በንቃት በመጠበቅና ጠንካራ ወታደር በመገንባት ብቻ በተሟላ መልኩ እንደማይረጋገጥ ያስገነዘቡት አቶ ማስረሻ ፀጋዎችን ስራ ላይ በማዋል ከተረጅነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር የተጀመረው ርብርብ በዜጎች ላይ ቁጭት ከመፍጠሩም ባሻገር የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ ማስቻሉን ነው ያመላከቱት ።

እምቅ ተፈጥሯዊ ፀጋዎች በሚገኙቡት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዝናብ ላይ ጥገኛ በነበረው አዝመራ ሲገኝ የነበረው ምርት እዚህ ግባ የማይባል እንዳልነበረ ተጠቁሟል ።

የሥራ ባህልን ለማሻሻልና የማምረት አቅምን ለማሳደግ በተፈጠረው ንቅናቄ የመስኖ እርሻ ተጠናክሮ መቀጠሉን

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሃላፊው አቶ ማስረሻ በላቸው አስረድተዋል ።

በዋናዋና ሰብሎችና በሆርቲካልቸር አመታዊ የማምረት አቅምን እስከ 75 ሚሊየን ኩንታል ማሳደግ መቻሉን በመጥቀስ።

የግብርናው ሴክተር ሚና በኩንታል ምርት ከመሰብሰብ በላይ መሻገር ይኖርበታል ባይ ናቸው ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩና የግብርና ቢሮ ሃላፊው ግብርናው የሚያመነጨው ኢኮኖሚ ከዜጎች ከእጅ ወደ አፍ ህይወት ተላቆ ሀገርን በሚያሻግር መሰረት መገንባት መጀመሩን ነው አቶ ማስረሻ ያስረዱት።

የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ግብ ከመሳካቱም ባሻገር ገቢ ምርቶችን መተካት መቻላችን ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ስኬት ነው ብለዋል።

ሰፊ ርብርብና ያለዕረፍት መትጋትን የሚጠይቁ ተግባራት በጅማሮ ላይ መሆናቸውን በመጠቆም።