April 4, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የዋልያዎቹ ድል ለቀጣይ ጨዋታ አቅም ይሆነናል – አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ

መጋቢት 16፣ 2017 የዋልያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ትናንት ምሽት ጅቡቲን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ካሸነፉ በኋላ ጨዋታውን ማሸነፍ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል።

ድሉ ለቀጣይ ጨዋታዎች አቅም እንደሚሆናቸው ጠቅሰው፤ በጨዋታው ከግብ ጠባቂው አንስቶ እስከ ፊት መስመር ያሉ ተጫዋቾች የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ጅቡቲ ላይ ስድስት ጎሎችን በማስቆጠራችን ያለብንን የግብ ዕዳ መሰረዝ ችለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የሚገኙት ተጫዋቾች ትልቅ አቅም እንዳላቸው የገለፁት አሰልጣኙ፤ በሂደት ጥሩ ቁመና ያለው ቡድን መገንባት እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች በአንዱ ድል አድርጎ በሁለቱ ተሸንፎ በሶስቱ አቻ በመለያየት በ6 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ዋልያዎቹ በቀጣይ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከግብፅ እንዲሁም ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከሴራሊዮን ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡