ማሻ ፣ የመጋቢት 16፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም በማሻ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል ።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ ደንቦችን በማፅደቅ ለህዝብ ተጠቃሚነት ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ እንደቆየ ጠቁመዋል ።
በዚህም በግብርና ዘርፍ፣በከተማ ልማት ከመሬት አቅርቦት ጋር ተያይዞ በርካታ ተግባራት መኖራቸውንና፣በእንሰት ምርት በስድስት ወር ውስጥ የተሻለ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል ።
በመንገድ ዘርፍም የተሻለ ስራ መሰራቱን የገለፁት ዋና አፌ ጉባኤ ለቀጣይ ውጤታማነት የምክር ቤቱ አባላት አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ ጠቁመዋል ።
በጉባኤው የባለፈው ጉባኤ ቃለ -ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣የአስፈጻሚ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ የእስካሁን አፈፃፀምና የቀሪ ወራት የጣቢያው ዕቅድ ቀርቦ ገምግሞ ከማፅደቅ ባለፈ ምክር ቤቱ ሹመትን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚተላለፍም ተናግረዋል ።
በጉባኤው ላይ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ከሁሉም መዋቅር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
More Stories
የዘመናት የማሻ ከተማና አካባቢው ህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት አቅርቦት ችግር የሚፈታ የሳብስቴሽን ግንባታ አልቆ መብራት የማብራት ሙከራ ስራ በስኬት ተጠናቀቀ
የለውጥ ዓመታቱ በፖለቲካ ምህዳራችን አካታችነትና አቃፊነት የተረጋገጠበት ነው- አደም ፋራህ
የሸካ ንጉስ ቴቺ ቄጃቺና የምክራቾ አባላት በማሻ ወረዳ ከሚገኙ የጎሳ መሪዎች ጋር ዉይይት አካሄዷል።