April 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በክልል ብዝሃ ዋና ከተማ ቴፒ ለሚነገነቡ የክልል ተቋማት ቢሮ ህንጻዎች ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አስቀመጡ።

ማሻ ፣ የመጋቢት 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፣የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት፣ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት ያለመ ተከታታይ ጥያቄ መሰረት በማድረግ የተደራጀ ክልል መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ክልሉ ከተቋቋመ ወዲህ በመንገድ፣በውሃ፣ በጤና እንዲሁም በግብርናና ለሎች ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የህዝብና የመንግስት አገልግሎት ለማሳለጥ በአራቱም ዋና የብዝሀ ከተሞች የክልል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ለመጀመር መሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ተግባር ላይ እንደሆኑ ገልፀው ለዚህም ከ2 አመት በላይ ጥናት መደረጉን ጠቁመዋል ።

ተቋሙ የጋራ በመሆኑ የዞንና የከተማ መዋቅር ለግንባታ ቦታ በማዘጋጀት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው ይህን ግንባታ ከዳር ለማድረስ ሁሉም የድርሻውን እንድወጣ ጠቁመዋል ።

የክልል ቢሮ መገንባት በአንድ ቦታ ሚቹና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ፣ለከተማ ውቤትም የድርሻውን የሚወጣ እንዲሁም ለብዙዎች የስራ እድል የሚፈጥር እንደሆነም ገልፀዋል ።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች ፣የሀይማኖት አባቶች በሰሩት ቁርጠኝነት የሰፈነውን የከተማ ሰላም ማፅናት ያስፈልጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ለከተማ ልማትና እድገት የኢንቨስትመንት መኖር ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ የመጣውን ሰላም በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አበበ ማሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መመስረት ምክንያት የሆነው ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ በመሆኑ ፓርቲ በሰጠው ትኩረት ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል ።

የህንፃ ግንባታ ለበርካታ ዜጎች ስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ለከተማ ውቤት ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል።

የክልል ህንፃ ግንባታ የሚቀመጥበት ቦታ ከይገባኛል ነፃ መሆኑን ገልፀው ግንባታው እስክጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የዞኑ መንግስት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚና መሰረተ ልማት ጉዳዮች አማካሪ ዶክተር እንጂነር ምትኩ በድሩ በበኩላቸው ግንባታው ከ670 ሚልየን ብር በላይ በጀት የሚጠናቀቅ መሆኑን ገልፀው በሁለት አመት ግዜ ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል ።

የከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው የህንፃ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ በመቀመጡ መደሰታቸውን ገልፀው ይህም ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።

የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነሥርዓት ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልል ርዕሰ መስተዳድር ማህረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ፣የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የሸካ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ስነስርዓት በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች ምርቃት የተጠናቀቀ ሲሆን በክልሉ የተጀመረው መሰረተ ልማት በጋራ መተባበር ተጠናቀው ለፍፃሜ እንድደርስ መልካም ምኞታቸውን በምርቃታቸው ገልጸዋል ።