መጋቢት 14፣ 2017 በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር መሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
በዚህም በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ንግስት ጌታቸው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።
አትሌት ንግስት ርቀቱን 1 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው።
በባለፈው ዓመት በግላስኮው በተደረገው የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረችው አትሌት ጽጌ ዱጉማ ትልቅ ግምት ብሰጣትም ውድድሩን 6ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
አትሌት ፅጌ ርቀቱን በ2 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ ከ76 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው ውድድሩን የጨረሰችው።
More Stories
በማሻ ወረዳ በህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ለተከታታይ 5ቀን ስካሄድ የነበረው የእግርኳስ ውድድር ፍጻሜውን አግኝተዋል።
የዋልያዎቹ ድል ለቀጣይ ጨዋታ አቅም ይሆነናል – አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ
ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም 3ኛ በመሆን አጠናቀቀች