April 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ቻይና አቀና

ማሻ ፣ የመጋቢት 10፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) በፈረንጆቹ ከመጋቢት 21 እስከ 23 ቀን 2025 በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ወደ ቻይና ናንጂንግ ሌሊት ላይ አቅንቷል።

ቡድኑ 12 አትሌቶች፣ ሁለት አሰልጣኞች፣ አንድ ቡድን መሪ፣ አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ እና አንድ ፊዝዮቴራፒስት ያካተተ ነው።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ መሀመድ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህንጨምሮ ሌሎች የፌዴሬሽኑ አመራሮች ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ለቡድኑ ሽኝት ማድረጋቸውን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።

ፋና