March 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፓትሪስ ሞትሴፔ የካፍ ፕሬዚዳንት በመሆን በድጋሚ ተመረጡ

ማሻ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ፓትሪስ ሞትሴፔ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ሆነው ለሁለተኛ ጊዜ ያለምንም ተቀናቃኝ ተመርጠዋል።

ደቡብ አፍሪካዊው የ63 ዓመቱ የወቅቱ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ በድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ እስከ 2029 ድረስ ካፍን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ።

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ካይሮ ላይ በተካሄደው የካፍ ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፓትሪስ ሞትሴፔ ለተጨማሪ አራት ዓመት የካፍ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚቆዩ ተረጋግጧል፡፡

ሞትሴፔ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ የካፍ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ፋና