March 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የ1 ሺህ 446ኛው የሐጅና ዑምራ ጉዞ የምዝገባ ጊዜ ተራዘመ

ሻ ፣ የመጋቢት 03 ፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የ1 ሺህ 446ኛው የሐጅና ዑምራ ጉዞ የምዝገባ ጊዜ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የተራዘመው የምዝገባ ሒደት ከትናንት ጀምሮ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ነው የተገለጸው፡፡

ምዝገባው የተሰጠው የጊዜ ገደብ በቂ አለመሆኑ በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ መራዘሙ ተገልጿል፡፡

ቀኑ የተራዘመው ፍላጎት ያላቸው ሐጃጆችን ለማስተናገድ በማለም መሆኑን የጠቆመው ምክር ቤቱ ÷ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በተሰጠው ጊዜ እንዲመዘገብ ጥሪ አቅርቧል።

ፋና