March 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የፆታ እኩልነትን በማረጋገጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባ ተገለፀ ።

ማሻ ፣ የመጋቢት 03 ፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) የሸካ ዞን ሴቶች፣ህፃናት፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ተግባር አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ የምክክር መድረክ በማሻ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የሸካ ዞን ሴቶች፣ህፃናት፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ከበደ እንደገለፁት በዞኑ የፆታ እኩልነትን በማረጋገጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የየመዋቅሩ ኃላፊዎች እንደገለፁት የሴቶችንና ህፃናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ መቻሉን፣የወጣቶች ማካተት ንቅናቄና ተሳትፎና ለሎች ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ በጠንካራ ጎን አንስተዋል ።

በአስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ማነስ፣የሴቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ስራ ዝቅተኛ መሆን፣የሴቶች የመሬት ባለቤትነት መረጃ የተጋነነ መሆን፣የስራ አጥ ወጣት ልየታ ያለመደረግና የመሳሰሉት አጀንጃዎች ላይ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ምክክር እየተደረገ ነው።