አየር ሃይሉ 167 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለመምታት በካሄደው ዘመቻ ነው 106 ድሮኖችን መትቶ መጣል የቻለው፡፡
ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ በዩክሬን ኦዴሳ፣ ኪየቭ፣ ሱሚ እና ቼርካሲ ግዛቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ርምጃ እንደተወሰደባቸው መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ÷ሩሲያ የወደብ ከተማ በሆነችው ኦዴሳ በፈጸመችው ተዳጋጋሚ ጥቃት ከ160 ሺህ በላይ ዩክሬናዊያን የሃይል አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡
አየር ሃይሉ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ የወሰደው የመከላከል ርምጃም ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንደሚቀንስ አመላክተዋል፡፡
ፋና
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ