February 21, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከእንግሊዝ መንግሥት የ12 አምቡላንሶች ድጋፍ ተረከበ

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በኢትዮጵያ የሚገኙት የእንግሊዟ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር በሀገሪቱ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት የተገዙ 12 አምቡላንሶችን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስረክበዋል።

አምቡላንሶቹን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ተረክበዋል።

አምቡላንሶቹ ለእናቶችና ህፃናት አስቸኳይ ሰብዓዊ አገልግሎት የሚውሉ የህክምና ግብዓቶችን ያሟሉ መሆናቸውም ተመላክቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሰብዓዊ ተግባራትን የጎበኙ ሲሆን ከማኅበሩ አመራሮች በትብብር በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።