February 21, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

የማሻ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ አድሳለም ገብሬ በመድረኩ እንደገለጹት ምክር ቤቶች ህገ-መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ሕግ-አውጭ ፤ሕግ-አስፈፃሚ እና ሕግ-ተርጓሚው ያከናወኗቸውን ተግባራት ለሕዝብ ቀርቦ የሚገመግምበት መሆኑን ተናግረዋል ።

ጉባኤውም የማሻ ወረዳ ምክር ቤት ያለፈውን መደበኛ ጉባኤ ቃሌ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣ የቀረበ ሹመት ማፅደቅን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችና ምክክሮች ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

በወረዳው ባለፉት ግማሽ በጀት ዓመትም የተከናውኑ አፈፃፀም ሪፖርት በሚመለከታቸው ባለድሪሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ።

ጉባኤውም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል ።