February 21, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አገራቸው ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት በተካሄደው የሳውዲ አረቢያ የሰላም ንግግር ላይ እንድትገኝ አለመጋበዟ የሚያስገርም ነው ማለታቸውን ተከትሎ ትራምፕ ጠንከር ያለ ወቀሳ አቅርበዋል።

የዩክሬን ምላሽ ያልጠበቁት እንደሆነ የገለፁት ትራምፕ፤ ለጦርነቱ ጅማሮ ዩክሬንን ተጠያቂ አድርገው አገሪቱ “ስምምነት ላይ መድረስ ትችል ነበር” ብለዋል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ይህን ማድረግ ይችሉ ነበር፤ ችግሩ በቀላሉ ሊፈታ ይችል ነበር ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ፥ ዩክሬን ጦርነቱን መጀመር አልነበረባትም፤ ስምምነት ላይ መድረስ ትችል ነበር ብለዋል።

ይህም ከሞላ ጎደል ሁሉንም መሬት ያስገኝላት ነበር፤ ሰዎች አይሞቱም ነበር፣ ከተሞችም አይፈርሱም ነበር ሲሉ ነው ትራምፕ የተናገሩት።