February 21, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛመደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነዉ ፡፡

በጉባኤው የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የአፈጻጻም ሪፖርት በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመቅረብ ላይ ይገኛል ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክርቤቱ አባላት ባቀረቡት የ6 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት በኢኮኖሚው ልማት ዘርፍ የተሻሉ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል ፡፡

ርዕሠ መስተዳድሩ ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል፡-

👉 በመኸር የግብርና ሥራዎች አዝመራ በተከናወነ ተግባር 384 ሺህ 786 ሄክታር የማሣ ሽፋን ተከናውኗል

👉 በተሰራው የግብርና ልማት ስራዎችም ከ17 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል።

👉 ለምርትና ምርታማነት መጨመር 145 ሺህ 909 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ቀርቦ ተሰረጭቷል ፡፡

👉 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል ነባርና አዲስ የሚለሙ በቁጥር 1,161 ንዑስ ተፋሰስ በመለየት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

👉 በክረምት ተከላ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው 145 ሚሊዮን 628 ሺህ 40 ችግኞች በንቅናቄ፣ ተከላ ተከናውኗል

👉 በአንድ ጀምበር ተከላ 24 ሚሊዮን 532 ሺህ 365 ችግኞችን የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ መትከል መቻሉ።

👉 20 ሺህ 700 ቶን የማር ምርት ማምረት መቻሉ

👉 በበጀት ዓመቱ አጋማሽ የታጠበና ያልታጠበ በድምሩ 25 ሺህ 47 ቶን የቡና ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል

👉 21ሺህ 877 ቶን የተለያየ ዓይነት የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል

👉 2ሺህ 813 ቶን የሻይ ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ መቅረብ ተችሏል

👉 ክልላዊ የደን ሽፋንን በመጨመር ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ 834 ሄ/ር በህገ ወጥ መንገድ የተወረረ ደን መሬት ወደ መሬት ባንክ የማስመለስ ሁኔታ ተፈጥሯል

👉 የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድና ዕድሳት አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ተከናውኗል በዚህም ከካፒታል ምዝገባ አንፃር ብር 7,243,047,962 ተመዝግቧል፡፡

👉 ነዳጅ ምርት አስተዳደርና ስርጭት በ 31 የነዳጅ ማደያዎች 14,047,091 ሊትር ቤንዚን እና 47,992,288 ሊትር ናፍጣ ቀርቦ ለተጠቃሚዎች ተሰራጭቷል፡፡

👉 የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉን ተከትሎ ምርት ባከማቹና አግባብ ያልሆነ ዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎችና የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ ዕርምጃ በመዉሰድ ዋጋ የማረጋጋት ሥራ መሰራቱ

👉 252 የንግድ ድርጅቶች በህገወጥ ንግድ እንቅስቃሴዎች በመሳተፋቸው አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰድ ተችሏል

👉 የኢንቨስትመንት ስራዎች አፈፃፀምን በሚመለከት በኢንቨሰትመንት ዘርፍ አዲስ ፍቃድ በግብርና 30 ፤ በኢንድስትሪ 10 እና በአገልግሎት14 ተከናዉኗል፡፡

👉 54 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱ ፕሮጀክቶች 4 ነጥብ ቢሊየን ብር ካፒታል ተመዝግቧል፡፡

👉 በክልሉ በ5 ሚሊዮን ኮድረስ 11,020 ተመዝግበው በመማር ላይ ይገኛሉ።

👉የክልሉን ዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በክልሉ ላሉ የመንግስት ተቋማት 2 ድረ-ገጾችን ዲዛይን ማድረግ ተችሏል፡፡

👉 የገቢ አሰባሰብ ስራን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማሳለጥ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ትግበራ 115 ግብር ከፋዮች ማሽኖችን ገዝተዉ እንዲጠቀሙ ተደርጓል

👉 በክልሉ 5,788 የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዩች ዉስጥ 39.58 በመቶ የሚሆኑት ማሽን ተጠቃሚ ሆነዋል

👉 በመደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በግማሽ ዓመቱ 5 ቢሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 4ነጥብ 5 ቢሊየን (90.02%) መሰብሰብ ተችሏል ስሉ በሪፖርታቸዉ አቅርበዋል።

ዘገባው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው