February 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፕሬዝዳንቱ ሃቪየር ሚሌይ የአርጀንቲናን ከዓለም የጤና ድርጅት የመልቀቅ ሂደት ለማስጀመር በመጪዎቹ ቀናት ትዕዛዝ ይፈርማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ይፋ የተደረገው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከዓለም አቀፉ የጤና ተቋም እንድትወጣ የሚያደርግ ሂደት የሚያስጀምር ትዕዛዝ ከፈረሙ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው።

ሁለቱ መሪዎች ከዚህ ቀደም አንዳቸው ለሌላኛቸው ያላቸውን አድንቆት ገልጸው ነበር። ፕሬዝዳንት ሚሌይ የትራምፕን በድጋሚ መመረጥ “በታሪክ ትልቁ ፖለቲካዊ መመለስ” ሲሉ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ሚሌይን “የእኔ ተወዳጅ ፕሬዝዳንት” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

#BBC