February 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የጥርስን ጤና መጠበቅ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት። የጥርሳችንን ንፅህና መጠበቅ መልካም የአፍ ጠረን እንዲኖረን ከማድረጉ ባለፈ የድድ እና ከአፍ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ በሽታዎችን እንደሚከላከል የጥርስ ሀኪሞችን አናግሮ ሲኤንኤን ዘግቧል።

በጥርስ ላይ የሚገኙ ባክቴሪያዎች አሲድ የሚያመነጩ ሲሆን ይህም ጥርስ እንዲጎዳ የሚያደርግ ነው። ውሎ ሲያድር ደግሞ የጥርስ መቦርቦርን እንደሚያስከትል ዶክተሮቹ ይገልጻሉ።

የጥርሳችንን ንፅህና በምንጠብቅበት ወቅት ከጥርስ ብሩሽ በተጨማሪ የጥርስ ማጽጃ ክርን መጠቀም እንደሚያስፈልግም ይናገራሉ።

ጥርስን መቦረሽ 60 በመቶ ንፅህና እንደሚሰጥ እና የጥርስ ማፅጃ ክር በበኩሉ 40 በመቶ እንደሚይዝም አስረድተዋል።